የእቃ ቁጥር | የእቃው ዓይነት | ብዛት | የአንዱ ዋጋ (በብር) | ጠቅላላ ዋጋ (በብር) |
---|---|---|---|---|
1 | ፍላኔል ጨርቅ | 1/4 ሜትር | 60 ብር | 15 ብር |
2 | ፎጣ | 60 * 20 ሳ.ሜትር | 10 ብር | |
3 | መቀሶች | 15 | 15 ብር | |
4 | ሜትር | 15 | 15 ብር | |
5 | የሚጣሉ ፓድ | 1 | 3 ብር | |
6 | ሻንጣዎች ፣ መርፌዎች ፣ ክሮች / ፒኖች... | 15 ብር | 15 ብር |
ጠቅላላ ወጪ: 73 ብር
የዳንቴል ስራ በሃገራችንም ሆነ በመላው ዓለም የታወቀ የእጅ ሙያ/ስራ ነው፡፡ እናቶች ልጆቻቸውን ለማልበስ ለማስጌጥ እንዲሁም ሹራብ ፣ስካርቭ ፣ ኮፊያ ፣ካልሲ እና ሌሎችንም በመስራት ከራሳቸው አልፎ ለስጦታነት ይጠቀሙታል፡፡
የዳንቴል ስራን በትንሽ ገንዘብ ለመጀመር መቻሉ የበለጠ ተፈላጊ አድርጎታል የሚያስፈልጉን ነገሮች ኪሮሽ፣ ክር ፣ መቀስ እና መለኪያ ሜትር ናቸው።
የእቃ ቁጥር | የእቃው ዓይነት | የአንዱ ዋጋ (በብር) | ጠቅላላ ዋጋ (በብር) |
---|---|---|---|
1 | ኪሮሽ | 40 ብር | 40 ብር |
2 | ክር | 50 ብር | 150 ብር |
3 | መቀስ | 15 ብር | 15 ብር |
4 | ሜትር | 15 ብር | 15 ብር |
የመነሻ ዋጋ: 220 ብር
የዳንቴል ስራን ለመስራት ዋነኛውና መሰረታዊው ስራ ክርን ኪሮሽ ላይ በውል መቋጠር ነው፡፡
ክሩን ካዘጋጀን በኋላ መስሪያ አቅጣጫችን በቀኝ ክር በኩል ስለሆነ በግራ በኩል ትንሽ ክር በማስቀረት በቀኝ ያለውን ክር ላዩ ላይ እንደርብና ኪሮሻችንን ወደታች በማስገባት ከላይ የተደረበውን በስር በኩል ወደላይ እናወጣዋለን ከዚያም ኪሮሹ ውስጥ የገባውን ክር ሳብ በማድረግ
ለስራ ዝግጁ እናደርጋልን፡፡
በውል የተቋጠረ ክር ያለበትን ኪሮሽ ጫፉን ወደላይ በማድረግ ክሩን መጥለፍና ጫፉን በመዘቅዘቅ ክሩን ይዞ ኪሮሹ ባለበት ቀዳዳ ውስጥ አሾልኮ ማውጣት፡፡ አሁን አንድ ሰንሰለት ተሰራ ማለት ነው።
ከአንድ በላይ ሰንሰለት ለመስራት ከተፈለገ ይህን አሰራር በመከተል ክሩን በመጥለፍ በኪሮሹ ቀዳዳ በማሾለክ መደጋገም
ከኪሮሹ ቀጥሎ ሁለተኛው ሰንሰለት ውስጥ ኪሮሹን አስገብቶ ክር ጠልፎ ማስወጣት።
ከዚያ በድጋሚ ክር በመጥለፍ ኪሮሹ ላይ ባሉት ሁለቱ ክሮች መሃል አሾልኮ ማስወጣት ይህንኑ ስራ በሚቀጥለው የሰንሰለት ቀዳዳ ውስጥ በማስገባት መስራት።