እሌኒ ገብር መድህን
ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የተወለዱት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። የልጅነት እና ወጣትነት ጊዜያቸውንም ከኢትዮጲያ በተጨማሪ ኬንያ ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአራት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች እየተዘዋወሩ አሳልፈዋል፡፡ ስዋሂሊ ፣ እንግሊዝኛ ፣ አማርኛ እና ፈረንሳይኛ አቀላጥፋ ይናገራሉ ፡፡ ኬንያ ውስጥ ከሚገኘው ሪፍት ቫሊ አካዳሚ ከፍተኛ
ክብር ባለው ማእረግ ተመርቀዋል ፡፡ በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በተግባራዊ ኢኮኖሚክስ ፒኤችዲ ፣ በሚሺገን ስቴት ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እና በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን ደግሞ ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በ የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለሀገራቸው አበርክተዋል።